የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(UNIDO) ማኔጅንግ ዳይሬክተር ሚስተር ጉንተር ቤገርን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ሐምሌ22/2017 ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(UNIDO) ማኔጅንግ ዳይሬክተር ሚስተር ጉንተር ቤገርን በቢሯቸው ተቀብለው በከርሃብ ነፃ ዓለማቀፍ ጉባኤ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ቃል የተገቡ ስምምነቶችን ወደ ተግባር ከመቀየር አንፃር ያለበትን ሂደት፣ የቻይና-አፍሪካ-ዩኒዶ የልህቀት ማዕከል (CoE)፣የፒሲፒ(PCP) ደረጃ II ስትራቴጂ ትብብር መፍጠር እና ሞጆ የቆዳ ከተማ ማዕከል(Mojo Leather City Center)ን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(UNIDO) ኢትዮጵያ ለአካታች እና ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን የምታደርገውን ጉዞ በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተና የማያቋርጥ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መላኩ ኢትዮጵያ በUNIDO ይሁንታ ያዘጋጀችው ከርሃብ ነፃ ዓለም አለማቀፋዊ ጉባኤ ስኬታማ ሆኖ ከመጠናቀቁም በላይ በርካታ አዎንታዊ ትምህርቶችና የስራ ትብብሮች የተገኘበት መሆኑን ገልፀዋል።

የቻይና-አፍሪካ-ዩኒዶ የልህቀት ማዕከል (CoE) ወደ ተግባር መግባቱ ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን፣ በአግሪ ቢዝነስ እና በታዳሽ ኢነርጂ ላይ በርካታ ፕሮፖሎችን ትኩረት ሰጥታ በማዘጋጀት እና በማቅረብ ስኬታማ ስራ እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትሩ በከርሃብ ነፃ አለማቀፍ ጉባኤ ላይ ቃል የተገቡ የስራ ትብብሮችና መልካም ተሞክሮዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር እንዲቀየሩ በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኩል ክትትል እንዲደረግ ጠይቀዋል ።

ኢትዮጵያ የፒሲፒ(PCP) ምዕራፍ 2 ስትራቴጂን ከአስር አመት የልማት እቅድ፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ እና የማኑፋክቸሪንግ ልማት ፖሊሲን ጨምሮ ከሀገራዊ ማዕቀፎች ጋር በማጣጣም ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ አቋም አላት ያሉት ሚኒስትሩ የUNIDOን የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

የሞጆ ቆዳ ከተማ ማዕከል በUNIDO ድጋፍ፣ የአዋጭነት ጥናቱ እና ESIA ተሻሽለው በይፋ በብሔራዊ የማኑፋክቸሪንግ ካውንስል እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን በመግለፅ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቦታ መለየቱንና የፌደራል መንግስት ለተዘጋጀው መሬት ካሳ በጀት መመደቡን ተናግረው የፓርክ ልማቱን የሚቆጣጠር የፕሮጀክት ትግበራ ክፍል (PIU) ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት አጀንዳዎች ላይ እያደረገ ላለው ጽኑ አጋርነት እና በዋጋ ሊተመን የማይችል ድጋፍ አመስግነዋል ።

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ሚስተር ጉንተር ቤገር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዓለማቀፍ ጉባኤዎችን የማዘጋጀት ብቃቷ ተወዳዳሪ የሌለውና ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል ስለመሆኑ ከርሃብ ነፃ አለማቀፍ ጉባኤ አንዱ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ በጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎችን፣ ቃል የተገቡ ስምምነቶችንና ሌሎችን ተያያዥ የቤት ስራዎችን ከተቋማቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር በመወያየት ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post