የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዩኒዶ ( UNIDO) በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው::

ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም(ኢሚ) በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዩኒዶ በተቀናጀ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ተወካይ አቶ አሰግድ አዳነ ገለጹ፡፡

አቶ አሰግድ ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አስራ አራት ኢንዱስትሪ ተኮር ፕሮጀክቶቹ መካከል አንዱ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መደገፍ እንደ መሆኑ መጠን በዘርፉ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ርሀብ አልባ ዓለም እዉን ማድረግ ይቻላል (WORLD WITH OUT HUNGER IS POSSIBLE) ዓለም አቀፍ ኮንፍረስ እንድታስተናግድ የተደረገው በተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ ተሞክሮ ስላላት መሆኑን ጠቅሰው ኮንፍረሱ ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄዱ በዩኒዶ ድጋፍ የተገነቡ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለዓለም ኢንቨስተሮች ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ርሀብ አልባ ዓለምን እውን ማድረግ ይቻላል (WORLD WITH OUT HUNGER IS POSIBLE) አለም አቀፍ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እንደምታካሄድ ይታወቃል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post