የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት (UNCTAD) በአፍሪካ ያደጉ ሀገራት ልዩ ፕሮግራሞች የአፍሪካ ክልላዊ ቢሮ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት (UNCTAD) በአፍሪካ ያደጉ ሀገራት ልዩ ፕሮግራሞች የአፍሪካ ክልላዊ ቢሮ ኃላፊ ዳያን ሳይንዞጋን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።
የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላቸው እና አብሮ ለመስራት ዕቅድ ማውጣቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በተለይም በንቅናቄው የአቅም ግንባታ ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ እና ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት ፍላጎት እንዳላቸው ያነሱት አቶ መላኩ አለበል በቅርቡ ባለሙያ ከውጪ በመላክ ይህን ስራ እንደሚጀምሩ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት (UNCTAD) በአፍሪካ ያደጉ ሀገራት ልዩ ፕሮግራሞች የአፍሪካ ክልላዊ ቢሮ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ድጋፍ በማድረግ በጋራ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት