የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የወጪ ምርት /export / አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው ( አቶ መላኩ አለበል)
ህዳር 30/2018 ዓ.ም ( ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት የአምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎች የህዳር ወር እና የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አምስት ወራት የኤክስፖርት አፈጻጸምን ሪፖርት ተገመገመ፡፡
የአምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎች የኤክስፖርት አፈጻጸማቸውን በማሻሻል የሀገራዊ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግ እና ምርታመነትን ለማረጋገጥ ባሳለፍነው የህዳር ወር የማኑፋክተሪንግ ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ የቴክስታይል እና ጋርመንት እንዲሁም የምግብ እና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የአምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎች የህዳር ወር የኤክስፖርት አፈጻጸም ጥሩ የሚባል እንደሆነ ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማንኛውም ጊዜ የኢንዱስትሪዎችን የኤክስፖርት አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ አምራቾች ችግሮቻቸውን በመፍታት የላቀ አፈፃጸም ማስመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተለያዩ አምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎችን ወክለው የተገኙ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የማምረት ስራችን ጥራትና ተወዳዳሪነትን ያሟሏ ሆኖ እንዲከናወን ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተል ባለፉት አምስት ወራት የውሃና የመብራት ችግር የተፈታ መሆኑን በመጥቀስ ሌሎች የዘርፉ ችግሮችም በተቀናጀ መልኩ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።