ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም (ኢ.ሚ) እንደ ሀገር የተጀመረዉ ብሔራዊ የምግብ ማበልጸግ ፕሮግራም የሚታይ ለዉጦች እያመጣ ነዉ /አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ/

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ከሳንኩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፌሊክስ ብሩክስ ቸርች ጋር ከዚህ ቀደም ለምግብ ማበልጸግ የተፈረመዉን ሰነድ መሰረት በማድረግ ያለበትን ሂደት ለመገምገም እና በቀጣይ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዎል።

ዉይይቱ የጥቃቅን ንጥረ-ምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን በማጠናከር፣ በቴክኒክ አቅም ግንባታ፣ በተጠቃሚዎች ግንዛቤ ፈጠራ እና ጥናትና ምርምር ላይ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታዉ ሳንኩ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቅን ንጥረ ነገሮችን ለማምረት ቃል በገባዉ መሰረት ግንቦት ወር ሀገር ዉስጥ ማምረት እንደሚጀምር እና ይህም ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ ወጪን ለመቀነስ እና ብሔራዊ የምግብ ማበልጸግ ፕሮግራምን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም አንስተዎል።

እንደ ሀገር በተጀመረዉ ብሔራዊ የምግብ ማበልጸግ ፕሮግራም በአስገዳጅነት ፋብካሪዎች የምግብ ዘይት፣ ስንዴ ዱቄትና የጨው ምርት በቫይታሚንና ማዕድን የበለጸጉ እንዲሆኑ በማድረግ የሚታይ ለዉጦች መምጣት እንደቻለም አቶ ታረቀኝ ገልጸዎል።

አያይዘዉም በሀገር ዉስጥ የሚመረቱትን ብቻ ሳይሆን ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የምግብ ምርቶችም የሚፈቀዱት በቫይታሚንና በማዕድን የበለጸጉ መሆናቸዉ ሲረጋገጥ እንደሆነም ሚኒስትር ዴኤታዉ ተናግረዎል።

ምግብን ማበልፀግ የአመጋገብ ጥራትን ለማሻሻልና ለጤና ጠቃሚ እንዲሆን ተጨማሪ አልሚ ንጥረ-ነገሮችን በመጨመር የተመጣጠነ የምግብ እጥረትን መከላከልን አላማው ያደረገ ነውም ብለዎል።

በመጨረሻም በአንድ ሀገር ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ለዜጎች በማንኛውም ጊዜ የምግብ አቅርቦትና ተደራሽነትን ማረጋገጥና ጥራቱ፣ ደህንነቱና የንጥረ-ምግብ ይዘቱ የተሟላ ምግብ መመገብ ወሳኝ በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነዉ ሲሉም አቶ ታረቀኝ አክለዎል።

Share this Post