በአምራችነት የተደገፈ የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ ካልተቻለ የኢትዮዽያ ነፃነት ሙሉ አይሆንም ( ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል)

በሀገር አቀፍ ደረጃ አምራችነት ቀን ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነዉ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አምራች ለማድረግ ከእያንዳንዱ ግለሰብ ምርታማነት ጀምሮ የተቛማትን ውጤታማነትና መደጋገፍ፣የሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላትን የነቃ ተሣትፎን ይጠይቃል ያሉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንደሀገርም አምራችነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በርካታ ስራዎች እየተሰራበት ያለ ጉዳይ መሆንንም ገልፀዋል። በአምራችነት የተደገፈ የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ ካልተቻለ የኢትዮጵያን ነፃነት የተማላ አይሆንም ያሉት ሚንስትራ ቀደምት አያቶቻችን ያፀንዋትን ሀገር በየተሰማራንበት ዘርፍ ጊዜው የሚጠይቀውን የአምራችነት፣ የታታሪነት፣ የትጋት አርበኝነት በመላበስ አገራችንን የማቆም፣ ለራስ የመብቃት እና ለሌሎች የመትረፍ ህልም በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

Share this Post