የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለሀገራዊ የኦኮኖሚ እድገት ፣ተወዳዳሪነትና ለብልጽግና መሰረት መሆኑ ታምኖበት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ======
መጋቢት 19/2018 ዓ.ም (ኢሚ) ኢንዱስትሪያላዜሽን የሚረጋገጠው በህብረተሰቡ ባለቤትነት፣ በግሉ ዘርፍ መሪነት እና በመንግስት የራስን የተቆጠረ የስራ ድርሻና ኃላፊነትን በመወጣት ነው
መንግስት በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት፣ ተወዳዳሪነትና ብልጽግና ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው ብሎ ከለያቸው ዘርፎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አንዱ መሆኑን የገለጹት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ዘርፉ በሀገራዊ የእድገት አማራጭ ላይ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ከህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል ፡፡
ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረትም የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅቶች ላይ ክለሳ መደረጉን በዚህም ኢትዮጵያን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የበለጸገች እና የአፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ሀገር የማድረግ ግብ ያለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን አቶ ታረቀኝ ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪያላዜሽን ጽንሰ ሃሳብ በርካታ ጉዳዮችን አካቶ የያዘ መሆኑንና ለአብነትም ከሀገራዊ ባለሃብቱ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኘውን የተማረና የሰለጠነ አምራች ዜጋ እና ሌሎችንም ያካተተ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህም የሚረጋገጠው በህብረተሰቡ ባለቤትነት፣ በግሉ ዘርፍ መሪነት እና በመንግስት በኩል የራስን የተቆጠረ የስራ ድርሻና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ዘርፉን ለውጪና ለሀር ውስጥ ባለብቶች ምቹ በማድረግ ረገድ በመንግስት በኩል በርካታ መደላለድሎችን በመፍጠር ለውጦች እየመጡ ይገኛል ያሉት አቶ ታረቀኝ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን በተለያዩ ኢኒሼቲቮች ለመፍታት በተደረገው ጥረት የኢትዮጵያ በታምርት እንዱ ማሳያ መሆኑንን አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ዓላማ ያለው መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህም በተለያዩ ተግዳሮት አማካኝነት የማምረት አቅማቸው የተዳከመ 917 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ምርት ሂደት በመመለስ፣ 46 በመቶ የነበረው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ወደ 66.3 በመቶ በማሳደግ፣ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት፣ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻን በማሳደግ፣በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራን በማጠናከር፣ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስፋት እና የሀገር ምርትን የመጠቀም ዝንባሌን እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ ንቅናቄው የተጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤታማ በማድረግ ረገድ በተለይም በንቅናቄው የመጀመሪያ የግንዛቤ የማስጨበጥ ምዕራፍ የመገናኛ ብዙሃን አካላት የጎላ ሚና እንደነበራቸው ጠቁመዋል፡፡