የአምራች ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያሳየ የመስክ ጉብኝት ነዉ
የካቲት 22/2018 ዓ.ም (ኢሚ)የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካዉንስል በሸገር ሲቲ እና በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዎል።
በጉብኝቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ እና የካዉንስሉ ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ የካዉንስሉ አባላት የሆኑት የተቋማት ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች የተገኙ ሲሆን የአምራች ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያሳየ የመስክ ጉብኝ እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴእታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልጸዎል።
በጉብኝቱ በተለይም ዉስን የነበሩ የብረት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች በሰፊዉ መስፍፍታቸዉን ያሳየ፣ ዘርፉ እየተነቃቃ መሆኑን በተግባር ያመላከተ እንደሆነ የገለፁት አቶ ታረቀኝ ለአምራች ኢንዱስትሪ ማነቆ ከሆኑት መካከል የፓኬጂንግ ኢንዱስትሪዉ አንዱ ሲሆን በዛሬዉ ጉብኝ ግን ችግሩን ሊፈታ የሚችል ተስፋ ሰጪ ኢንዱስትሪ አይተናል ብለዋል።
አክለዉም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በብዛት እና በጥራት እያደገ መምጣቱን በተግባር ያዩበት የመስክ ጉብኝት እንደነበር ገልጸዋል።
በመጨረሻም ካዉንስሉ በመስክ ምልከታ ያጋጠሙ ችግሮችን ቆጥሮ በመዉሰድ የሚመለከታቸው ተቋማት የየራሳቸውን ኃላፊነት ወስደው እየሰሩ እንደሆነ እና ወደ ፊትም ይህ የቅንጅት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ታረቀኝ ተናግረዋል።