አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያለውና ዕሴት የተጨመረበት ምርት ይዘው መቅረብ አለባቸው(አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)
የካቲት 18/2018 ዓ.ም(ኢ.ሚ)የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኢትዮጵያ ታምርት አዲስ አበባ ትበልፅግ በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ባዘጋጀው የምርት ዐውደ-ርዕይ የጉብኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡
የኢንዱስትሪ ዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የሚሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያለውና ዕሴት የተጨመረበት ምርት ለማቅረብ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ዘንድሮ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ካለፉት ዓመታት በላቀ መልኩ እጅግ በጣም በርካታ የውጭ ጎብኝዎች እንደሚጎበኙት የተናገሩት አቶ ታረቀኝ ሴቶችን ፣ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ምርት ያመረቱና ብዙ ጎብኝ ለሚጎበኛቸው ተሳታፊ አምራች ኢንዱስትሪዎች ልዩ የማበረታቻ እንደሚያዘጋጅ አብራርተዋል፡፡
ዐውደ-ርዕዩ የካቲት 13/2018 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን እስከ የካቲት 21/2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡
የበጉብኝት መርሀ ግብሩ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡