የአምራች ላኪ ኢንዱስትሪዎች የስድስት ወር ኤክስፖርት አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት አምራች ፋብሪካዎች መንግስት በፖሊሲ፣ በብቃት፣ በጥሬ እቃ አቅርቦት እና በሌሎችም ሴክተሩ ላይ አለብን የምትሉትን ችግሮች በዋናነት ለመፍታት እየሄድንበት ያለው ርቀት ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትል የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ኤክስፖርት አፈፃፀም ከፍ በማድረግ በአጠቃለይ የሃገሪቱ ጊቢ ላይ የራሱን አበርክቶ እንዲያደርግ እና እንደ ሃገር ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን ያህል የ እንዲወጣ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

አቶ መላኩ አክለውም በቅርበት ከእናንተ ጋር በመነጋገር ለችግሮቻችሁ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ውጤታማ የምትሆኑበትን መንገድ እያመቻቸን ያለነው አንዳድ ፋብሪካዎች ምርታቸው ካለፈው አመት አፈፃፀም አንፃር ከፍተኛ ሆኖ ሳለ ኤክስፖርት አፈፃፀሙ ዝቅ ያለበት ምክንያት ተፈትሾ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ለአምራቾች የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግና ተከታታይ ውይይቶችን በማካሄድ የሚገጥሟቸውን ችግሮች በመፍታት በሚቀጥለው የስድስት ወር ኤክስፖርት አፈፃፀሙን ውጤታማለማድረግ ይሰራል።

በውይይቱ ከስድሳ በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን መንግስት በቅርበት እየተከታተለ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሄደበትን እርቀት አናመሰግናለን ሲሉ ገልፀው እኛም እንደ ሃገር የሚጠበቅብንን ኢኮኖሚያዊ አብርክቶ ለመወጣት ተግተን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

Share this Post