የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጀርመን ኢንባሲ የልማት ትብብር ኃላፊ አንጃ ፖውልስ የተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ
ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም (ኢ.ሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጀርመን ኢንባሳ የልማት ትብብር ኃላፊ አንጃ ፖውልስ የተመራ ልዑክ ጋር አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ በተደረጉ ድጋፎች እና ወደፊት መደረግ ስላለበባቸው የድጋፍና ትብበር ስራዎች አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በውይይቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ለኤክስፖርት ምርቶች ትኩረት የሰጠ ፣ የስራ እድል ፈጠራን ፣የወጣቶችንና የሴቶችን ተሳታፊነትና ጥቅም የሚያበረታታ፣ ከአካባቢ ጋር የተዛመደ ኢንዱስትሪን ለመገንባት ራዕይ በመሰነቅ እየሰራች እንደሆነና በዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ሀገራችን ዘርፉን በማሳድግ ተጠቃሚ ለመሆን ለምታደረገው ጥረት የጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት(GIZ) እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው ዘረፉን ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም በኢንዱስትሪ ዘርፉ የሰለጠነ የስው ሃይል፣ የፋይናንስ፣ የሀይል እጥረት እና ሎጂሰቲክስ ከተግዳሮቶቹ መካካል ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑና እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጀርመን ኢንባሲ የልማት ትብብር ኃላፊ አንጃ ፖውልስ በበኩላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ ለማሳደግ ስትራቴጂ በመቅረጽ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገው ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ግልጽና ጥልቅ በሆነ መልኩ ለተደረገላቸው ገለጻ ሚኒስትሩን አመስገነው በቀጣይ በተመረጡ የትብብር መስኮች ላይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
የጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት (GiZ Ethiopia) ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ክላስተር አስተባባሪ ሚስተር ቬልተን ሄበርመህል፣ የጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት (GiZ Ethiopia) የፕሮግራሙ ኃላፊ ወይዘሮ አና ዋድማን ፣የጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት (GiZ Ethiopia)የስትራቴጂ አማካሪ ዶ/ር ዣን ባፕቲስት ዳሜስቶይእና የጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት (GiZ Ethiopia)የፖሊሲ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሙሴ ምንዳዬ በውይይቱ የተሳተፉ የልዑኩ አባላት ናቸው።