የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መካከለኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች እውቅና ሰጠ።

ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት አመት የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች የመደበኛ ስራዎች አፈፃፀምን በሶስት ዋና ዋና የመመዘኛ መስፈርቶች ማለትም ከአሰራር ስርዓት፣ ከቁልፍ ውጤት አመላካቾች እና ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንፃር በድምሩ በ30 ዝርዝር መመዘኛ ነጥቦች በማወዳደር በመካከለኛ አፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡት እውቅና ሰጥቷል ።

በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረትም ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በ2017 በጀት አመት መካከለኛ አፈፃጻም ካዝመዘገቡ ክልሎች ከአንድኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማታቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮች ተቀብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post