በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አቶ መላኩ አለበል የተመራ ልኡክ ዳን ቴክኖ ክራፍት እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ የፋብሪካ ምልከታ እና ውይይት አካሄዱ ።

የካቲት 12/6/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ የፋብሪካ በየጊዜው እያደገ የመጣ ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች በሃገር ውስጥ በመተካት እየሰራ ያለ መሆኑን መረዳት ችለናል ያሉት የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ባዩት የስራ እንቅስቃሴ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ፋብሪካውን ከዕድሜው ካለው የሰለጠነ የሰው ሃይል ፣ ዲጂታል የአደረጃጀት ሰርዓት፣ በማኔጅመንት ፣ በፋይናስ ፣በማርኬቲንግ እና ባሉት የፋብሪካ ማሽኖች ማስተዋወቅ ቢቻል ከዚህ በላይ ሊያድግና ስራተኛው በሽፍት የሚሰራበት ፣ ፋብሪካው 24 ሰዓት ምርት የሚያመርትበት ፣ የሃገር ውስጥ ፍላጉትን አሟልቶ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ሊደርስ የሚችልበት ዕድል ነበር ሲሉ ገልፀዋል ።

አብረን በጋራ እየተነጋገርን ፋብሪካው ያለበትን ችግር እየፈታን እንሄዳለን ያሉት ሚኒስትሩ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ የምትሰሩበትን ነገር ለማመቻቸት እና ድጋፍ ለማድረግ የሚጠበቅብን ሁሉ እናደርጋለንብለዋል ።

የዳን ቴክኖ ክራፍት እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ ፋብሪካ መስራች እና ባለቤት ኢንጂነር ዳንኤል መብራሃቱ በበኩላቸው ፋብሪካው ከተመሰረተበት 1965 ዓ ም ጀምሮ መኪና በመገጣጠም ፣ ፋይል ካቢኒቶች ፣ ካዝና ፣ የሆስፒታል አልጋ ፣ ሊፍት እንደሚያመርት ገልፀው ሌሎችም የእንጨት ፣ የብረታ ብረት ፣ ምርት ውጤቶች አስራለን ሲሉ ገልፀዋል ።

ፋብራካው በሚያመርተው ሊፋት Iso 9001-2000 የጥራት ተሸላሚ መሆናቸውን የገለፁት ኢንጂነር ዳንኤል መንግስት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ፋብሪካውን በመጎብኘቱ አመስግነዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post