ዘላቂ አካታች እና ተወዳዳሪ አምራች ኢንዱስትሪ ለመገንባት የክልል መንግስት የሚያደርገው ክትትል እና ድጋፍ ወሳኝ ነው (አቶ ዳዊት አለሙ)
ጥር 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት በአካባቢና በአየር ንብረት ለውጥ ስራ ላይ ለተወከሉ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ቢሮ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ በአከባቢ ጥበቃ ፓሊሲዎች፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ የሃይል አጠቃቀም እንዲሁም ከአካባቢ እና ከአየር ብክለት የፀዳ የአመራረት ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ የክልል መዋቅር ሚና ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የፕርጀክቱ ኃላፊ አቶ ዳዊት አለሙ እንደገለፁት ያለንን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ መጠቀም ዘላቂና አካታች አምራች ኢንዱስትሪ ለመገንባት ከተቀረጹ የኢንዱስትሪ ፖሊሲው ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።
በቅርቡ መንግስት ያወጀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የአምራች ኢንዱስትሪው ሃይልን በብቃት እንዲጠቀም እና ያላስፈላጊ የሃይል ብክነትን ለመቀነስ የሚያነቃቃ በመሆኑ ከዘርፉ ለመቀነስ የታሰበውን 40 በመቶ የሃይል ብክነትን ለማሳካት ክልሎች ድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት