የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ምርምርና ሰርፀት ውጤታማ ሆኗል ( አቶ ዮናስ መኩሪያ )

ጥር 29/5/2017 (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት የፌዴራል እና የክልል የክላስተር ኮሚቴ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ምርምርና ሰርፀት ውጤታማ መሆኑን እና ከንቅናቄው ከተጀመረ ጀምሮ አበረታች ውጤት እየታየ መሆኑን በኢትዮጵያ ታምርት የአቅም ግንባታ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዮናስ መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተዘረጋው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጎን ለጎን የተቋቋመው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ብሄራዊ ካውንስል ፋብሪካዎችን በመለየትና በጥናት ላይ ተመስርቶ ችግሮችን በቅርበት በመመልከትና አፋጣኝ መፍትሄ በሚያገኙበት አግባብ ላይ አመራርና አቅጣጫ በመስጠት አበረታች ስራ ተከናውኗል ሲሉም አንስተዋል፡፡

አቶ ዮናስ የ10 ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪው ላይ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በመቅረፍ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት ስትራቴጂያዊ መፍትሄዎችን በመስጠት በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ መሆን ተችሏል ብለዋል፡፡

በትኩረት መሰኮች የአምራች ኢንዱስትሪ አካታችና ዘላቂ የማኑፋክቸሪግ ሰርዓት ምርትና ምርታማነትን፣ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ ተችሏል።

በዋና ዋና ግቦች የምርት ጥራት ማሻሻል፣ በገበያ ተወዳዳሪ በመሆን ለውጥ ማምጣት፣ በኢንዱስትሪ መካከል የክህሎት ልምድ ልውውጥ ማደረግ በተጨማሪም በሀገር ውሰጥ አምራቾች የሚመረቱት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የኢንዱስትሪ ምርቶችን የተጠቃሚዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ሰፊ ሰራ መሰራቱን አቶ ዮናስ ገልፀዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post