ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የፈጠረውን መነቃቃት መሰረት በማድረግ በክልል እና በከተማ አስተዳደር አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም የተለየ ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ነው (ዶ/ር አያና ዘውዴ)
ጥር 29/5/2017ዓ.ም (ኢሚ) የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የፌደራል እና የክልል የቴክኒክ ኮሚቴ እቅድ አፈጻጸም ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር አያና ዘውዴ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የፈጠረውን መነቃቃት እና ቅንጅታዊ አሰራር መሰረት በማድረግ በክልል እና በከተማ አስተዳደር አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም የተለየ ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልል እና ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ወረዳዎች ምን አይነት አቅም እና ጸጋዎች እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎች አሉ የሚለውን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዶ/ር አያና ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት