በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በርካታ ችግሮች ተፈተዋል (አቶ መላኩ አለበል)
ጥር 23/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ወደ ስራ ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ተንሰራፍተውና ስር ሰደው የቆዩ በርካታ ችግሮች መፈታታቸውን የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት እጅግ አበረታች ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የአምራች ዘርፉ ተኪ ምርትን እና የኤክስፖርት ምርቶችን በተፈላጊው መጠን እና ጥራት እንዲያመርት በማስቻል በኢኮኖሚው ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ጫና ከመቀነስ አልፎ ሀገራዊ ምርትን ከማሳደግ አኳያ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው በንቅናቄው በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተዘረጋው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጎን ለጎን የተቋቋመው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ብሄራዊ ካውንስል ሁኔታ ቀያሪ (game changer) ፋብሪካዎችን በመለየትና በጥናት ላይ ተመስርቶ ችግሮችን በቅርበት በመመልከትና አፋጣኝ መፍትሄ በሚያገኙበት አግባብ ላይ አቅጣጫ በመስጠት አበረታች ስራ ተከናውኗል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ያለንን የግብርናና የማዕድን እምቅ ሀብት በመጠቀም ኢንዱስትሪላይዜሽንን በገጠር አካባቢ በማስፋፋት ሰፊ የሆነ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች መነሻ የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ለመፍጠር ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ስራዎች ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ያሉት ሚኒስትሩ ይህንንም ስራ በቀጣይ በተለዩ በሁሉም ወረዳዎች ተግባራዊ እንዲደረግ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ዕድገታችን የኢትዮጵያን ማህበራዊ፣ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በአስገዳጅነት የማስቀየር አቅሙን ታሳቢ በማድረግ እንደ ተግዳሮት የሚታዩትን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የየሴክተሮች ምርትና ምርታማነት ክፍተት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ክፍተቶች በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስተሪዎች የመስሪያና መሸጫ ቦታ አቅርቦት ችግሮችን በመፍታት የኢትጵንያን የኢዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት