ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን እድገት እያመጡ ካሉ ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ የተረጋገጠ እውነታ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2015(ኢሚ)፦ ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን እድገት እያመጡ ካሉ ጥቂት ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻ 28 በመቶ መሆኑን በማንሳት፤ በዚህ በጀት ዓመት 8 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት እንደሚያመጣ ይጠበቃል ብለዋል።
የዘርፉ እድገት ዋነኛ ምንጭ የሆነው ኢንዱስትሪው ለአንድ ዓመት ያህል በተተገበረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስራ አቁመው የነበሩ ፋብሪካዎችን ወደ ስራ ማስግባት መቻሉን ተናግረዋል።
በማብራሪያቸውም በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚ እድገት 7 ነጥብ 5 በመቶ የሚመዘገብበት ይሆናልም ብለዋል።