የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለአቅመ ደካማ ዜጎች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን 4 ቤቶችን አስረከበ

ነሐሴ 25/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ለ4 አቅመ ደካሞች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን ቤቶችን አስረክቧል።

በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢኖቬሽንና ኢንደስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ግዚያት ሰው ተኮር ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።የበጎ ተግባር ስራ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ገንብቶ በማስረከቡ በተቋማቸውና በክልሉ ስም አመስግነዋል።

ዶክተር ሚልኬሳ ጃጋማ የሚኒስትሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲዩት ሀላፊና የሚኒስትሩ ተወካይ በስፍራው ተገኝተው እንደገለፁት መስሪያ ቤቱ ባለፉት ጊዚያት አቅመ ደካሞችን በመርዳት ተመሳሳይ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የተገነባው የአቅመ ደካሞች ቤት እስኪጠናቀቅ ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ አካላትን አመስግነዋል። በቀጣይ ሁሉም አካላት በመተባበርና በመተጋገዝ የሀገር ብልፅግናን እውን ማድረግ አለብን ብለዋል። የቤንች ሸኮ ዞን ስራ ክዕሎትና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው የለውጡ መንግስት ያስጀመረውን የሰው ተኮር ተግባር ከጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

ከዚህ ቀደም እንደነዚህ አይነት ተግባራት ወደታች በማውረድ አቅመ ደካማ ዜጎችን መርዳት ትኩረት ሳይጥ በመቅረቱ መለምድ አለመቻሉን ገልፀው በወረዳው ይህንና መሠል ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በር ከፋች መሆኑን የተናገሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ ናቸው።

የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል በ2015 በክረምት በጎ አድራጎት ስራ በስፍራው ተገኝተው ያስጀመሩት መሆኑ ተገልጿል።  በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል የክልልና የዞንና የወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ከቤት ግንባታ በተጨማሪ ለቀጣይ ድጋፍ የሚሆኑ የቁም እንስሳት እና አልባሳት እንዲሁም የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

Share this Post