የግብርና ምርቶችን የሚያቀናብሩና ዕሴት የሚጨምሩ ኢንዱስትሪዎች የእርስ በእርስ ትስስር መኖር የምርት ብክነትን ይቀንሳል( አቶ ሀሰን መሀመድ)

ግንቦት16/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምግብ ጥራትና ደህንነት ላይ በሚሰራ አርተር (ART-ER) ከተባለ የኢጣሊያ መንግስት ድርጅት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ደኤታ ክ አቶ ሀሰን መሀመድ የግብርና ምርቶችን የሚያቀናብሩና ዕሴት የሚጨምሩ ኢንዱስትሪዎች የእርስ በእርስ ትስስርና ቅንጅት የምግብና መጠጥ ደህንነትን ከማረጋገጡም በላይ የምርት ብክነትን እንደሚቀርፍ ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ዋና ዓላማ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚቀናበሩና የሚመረቱ ምግቦችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚቋቋሙ ቤተ ሙከራዎችን በተመለከተ የቅድመ ዳሰሳ ጥናት በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ገንቢ አስተያየት መሰብሰብ እንደሆነ በመርሀ ግብሩ ተብራርቷል፡፡

በቀጣይም የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ኢጣሊያ በመሄድ በግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚቋቋሙ ቤተ-ሙከራዎችን አስመልክቶ ተሞክሮ እንደሚቀስም የተገለጸ ሲሆን በውይይቱ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችና የልማት ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post