የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሐመድ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ዲላ መካከለኛ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ ።

ሚያዚያ 3/8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) አግሮ ኢንዱስትሪው የአቡካዶ ዘይት፣ ማር፣ የግብርና ውጤቶች፣ ቡና እና የአስሳት ተዋፆኦ እንዲያመርት ታስቦ መሰራቱ ተገልጿል ።

በፓርኩ ውስጥ ገብተው ወደ ስራ ከገቡት አምራቾች መካከል ሲዝ (siz) አግሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በቀን ሰላሳ ቶን የአቡካዶ ዘይት እና ቡና እያመረተ ወደ ውጭ እደሚልክ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል ። በተጨማሪም ከተረፈ ምርቱ የእስሳት ተዋዕፆ እና ኮፖዝ እንደሚያመርት ታውቋል ።

በጉብኝቱ ወቅት ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ እያጋጠሙ ላሉ ችግሮች መፍትሔ በመስጠት የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ጥላሁን ብርሃኑ እንዳሉት በቀጣይ ባለሃብቱ ፓርኩ ውስጥ በመግባት የወተት ተዋፆኦ እና ማር ምርት ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

http://linktr.ee/fdremoi

Share this Post