የፕላስቲክ ፎርምዎርክ ከእንጨት የሚሰራውን የግንባታ ግብዓት በመተካት የደን መጨፍጨፍን መቀነስ እንደሚያስል ተገለፀ፡፡ ወ/ሮ ካሳነሽ አያሌው

የካቲት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚና ባለቤት ወ/ሮ ካሳነሽ አያሌው ፋብሪካው በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የግንባታ ፕላስቲክ ፎርምዎርክ አምርቶ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እየተከለች ቢሆንም በሌላ በኩል ለእንጨት ፎርምዎርክ መስሪያ ዛፎች እንደሚቆረጡ አንስተዋል።

የፕላስቲክ ፎርምዎርኩ ከእንጨት የሚሰራ የግንባታ ግብዓትን በመተካት የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።

የእንጨት ፎርምዎርኮች ቢበዛ እስከ 5 ጊዜ ቢያገለግሉ ነው ያሉት ስራ አስኪያጇ ፋብሪካው በእንጨት የሚመረቱትን በፕላስቲክ በመተካት የደን መጨፍጨፍን ከመቀነስ ባለፈ ፎርሞርኮቹ ከ50 ጊዜ በላይ የሚያገለግሉ በመሆናቸው የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ይቀንሳል ሲሉ አብራርተዋል።

የፕላስቲክ ፎረምዎርኮች ከዚህ ቀደም ከውጪ የገቡ እንደነበር ያነሱት ወ/ሮ ካሳነሽ ይህም ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ የሚያሳጣ መሆኑን ገልፀዋል።

ምርቶቹ በሀገራችን ውስጥ መመረታቸው ከውጭ የሚገባውን ተመሳሳይ ምርት በመተካት በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post