"የስራ ስምሪት ማበልጸግ" በሚል መሪ ቃል 5ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ እና ቴክኖሎጂ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል፡፡

ህዳር 8/2015ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢ.ሚ)በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ255 ሺህ በላይ አዳዲስ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን አስታውሰው መንግስት ይህንን ተመልክቶ የአይሲቲ እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሁለቱ ምሰሶዎች እንደሆኑ በመለየት ወደ ስራ መግባቱ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ የሰለጠነ የሰው ሃይል፣ የተፈጥሮ ሃብት፣ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና የአህጉራዊ እና አህጉር አቀፍ ገበያዎች ተደራሽነት በተለይም የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ትልቅ የገበያ እድል የሚከፍት ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በማኑፋክቸሪንግ ኢንቨስትመንት ምቹ ያደርጋታል ብለዋል።

መንግስት ለግሉ ሴክተር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውሰው ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የንግድ አካባቢን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የዘርፉን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር እውን ለማድረግ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣ የገበያ ተደራሽነት፣ የመሬትና ፋይናንስ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

5ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ እና ቴክኖሎጂ የንግድ ትርዒት ከ10 በላይ የተውጣጡ የውጪ ሀገራት አምራቾች የጨርቃ ጨርቅ፣ የፈርኒቸር፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ቀርበዋል፡፡

የንግድ ትርዒቱ ለ5 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ6ሺ በላይ ጎብኚዎች እንደሚገኙበት ይጠበቃል፡፡

Share this Post