የኢትዮጵያ ታምርት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት የቴክኒክ ኮሚቴ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነዉ።
ጥር 29/5/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት የቴክኒክ ኮሚቴ እቅድ አፈጻጸም ግምገማ የፌደራል የኢትዮጵያ ታምርት ቴክኒክ ኮሚቴዎች እና የክልል ፍካል ፐርሰኖች በተገኙበት እየተካሄደ ነዉ።
በዚህ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በኢትዮጵያ ታምርት በግማሽ ዓመቱ ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም የቀጣይ ትኩረት መስኮች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል ።
የግምገማ መደረኩን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አያና ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረዎል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት