በላያ ኢንደስትሪያል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ያስገነባው የውኃ ፋብሪካ ተመረቀ።

ህዳር10/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢ.ሚ) በላያ ኢንደስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በሱሉልታ ከተማ የውኃ ፋብሪካ አስመርቆ ወደ ሥራ አስገብቷል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ፣ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ፣ የኦሮሚያ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሚሊዮን በቀለ እና ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Share this Post