በጥጥ አምራቾችና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ነው/ አቶ ሐሰን መሀመድ/

ህዳር12/2015ዓ.ም አዲስ አበባ(ኢ.ሚ)ከጥጥ አምራችና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ባለቤቶች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በውይይቱም በግብይት ስርዓት ውስጥ ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩ ከትርፍ በላይ ለማግኘት የሚሰሩትን ለማስቀረት አምራች ገበሬዎችንና ፍብሪካዎችን በቀጥታ ለማስተሳሰር እየተሳራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሀመድ አስረድተዋል፡፡

በተለያዩ መድረኮች የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የጥጥ ግብዓት ችግር አለብን ፣ የጥጥ አምራች ገበሬዎች በበኩላቸው ምርት የሚገዛን የለም የሚሉ ችግሮች ሲያነሱ እንደነበር እና በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ የደላላ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ጠቁመው የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራቾቹን ከፋብሪካዎች ጋር ለማስተሳሰር የሚረዳ ውይይት መደረጉን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል።

አምራቾችም ሆነ ፋብሪካዎች ሳይጎዱ የሚገበያዩበት ስርዓት በመፍጠር በሀገሪቱ የጥጥ ምርት ምርታማነት በማሳደግ ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው የጥጥ አምራቾችና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የሚነሷቸውን ችግሮች ለመፍታት ሚኒስትር መ/ቤቱ እየሰራ እንደሆነ ገልጸው ችግሮችን ለመፍታት ይረዳ ዘንድ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሪነት ኮሜቴ በማዋቀር ወደስራ ተገብቷል ብለዋል ፡፡

Share this Post