የእቃ ማከማቻ መጋዘን ደረሰኝ ስርዓት ለአርሶ አደሩ እና ለአምራች ኢንዱስትሪው ያለው ፋይዳ የጎላ ነው /ሀሰን መሀመድ

08/03/2015 ዓ.ም (ኢሚ) የግብርና ምርት የእቃ ማከማቻ የመጋዘን ደረሰኝ ስርዓት አርሶ አደሩ ለሚያመርተው ምርት ተገቢውን ዋጋ በሚፈልገው መንገድ እንዲያገኝ ያደርጋል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሀመድ የአምራች ኢንዱስትሪውን የጥሬ እቃ አቅርቦትና የፋይናንስ ችግር በመፍታት እንዲሁም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን የግብዓትና የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮች ለመፍታት የፋይናንስ ተቋማትን ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር ታስቦ በ1996 ዓ.ም የወጣው የመጋዘን ደረሰኝ ስርዓት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ጠቅሰው ስርዓቱ በሳለፍነው ዓመት ወደ ተግባር እንዲገባ በመደረጉ በፓይለት ተወስደው ተጠቃሚ የሆኑ አምራቾች ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ የመጋዘን ደረሰኝ ስርዓቱ እየተተገበረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እየተጫወቱ ባሉ የፋይናንስ ተቋማትና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በጋራ በመቀናጀት በቁርጠኝነትና በላቀ የአመራር ብቃት ውስጣዊ ጥንካሬን በማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ በተመለከተ ከባንኮች፣ ከክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች እና የስርዓቱን ለመጠቀም ፍላጎት ያሳዩ አምራቾችን ያሳተፈ ውይይት ተካሄዷል፡፡

Share this Post