የፕላስቲክ ጠርሙሶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ ወደ ምርት ለማስገባት ስምምነት ላይ ተደረሰ

ህዳር8/2015ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢ.ሚ) የፕላስቲክ ጠርሙሶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ በኢትዮጵያውያን እና ጣልያን ኩባንያዎች ተገንብቶ ወደ ምርት ለማስገባት ስምምነት ላይ መደረሱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል ፡፡

ፋብሪካው ከዘጠኝ ወራት በኃላ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ምርት ሂደት ሲገባ ከ10,000 እስከ 15,000ሺ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ እና የፕላስቲክ ጠርሙሶችን መልሶ መጠቀም በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅቶ በቀን 120ቶን ወደ ውጪ በመላክ ከ150,000ሺ በላይ ዶላር ማግኘት የሚያስቸል ነው ተብሏል ፡፡

Share this Post