የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢንዱስትሪ ለውጥ እና በኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ ያጋራ ምክክር እያደረጉ ነው፡፡

ጥቅምት25/2015ዓም አዲስ አበባ (ኢ.ሚ) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ የሚካሄደውን የአፍሪካን ኢንደስትሪላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ብዝሃነት የመሪዎች ጉባኤ መሰረት በማድረግ በኢኮኖሚ ብዝሃነት እና በኢንዱስትሪ ለውጥ ላይ ያተኮረ ውይይት በኒጀር ኒያሚ እያካሄዱ ነው፡፡

በውይይቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሃመድ ተሳታፊ ሲሆኑ አፍሪካ አንድነት ኮሚሽን ከሚመለከታቸው አጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በመጪው ኖቬምበር 20 /2022 ያዘጋጀው የአፍሪካን ኢንደስትሪላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ብዝሃነት የመሪዎች ጉባኤ መሠረታዊ ሃሳብም ሁሉን አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን የኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የግብርና እሴት ሰንሰለቶችን ማሳደግ የአፍሪካ የወጪ ንግድ ሚዛኑን የጠበቀና በዓመት ወደ 115 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የወጪ ንግድ ጥገኝነትን እንደሚቀንስ ተጠቁሟል፡፡

የክልልና አህጉራዊ የአግሪ ቢዝነስ ኢንዱስትሪዎች የእሴት ሰንሰለት መጎልበት የአፍሪካን ህዝብ ለመመገብና የአህጉሪቱንም የምግብ ዋስትና እንድታረጋግጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

Share this Post