አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት በማድረግ በጥራት፣ጊዜና መጠን የተለካ እንዲሆን አድርገው ማቀድ አለባቸው፡፡

ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል ካኪ የአይሲዙ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ ለማስቻል መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ስራ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መላኩ ሁሉም አምራቾች መዳረሻቸውን ሩቅና ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት በማድረግ የስራ ውጤታቸው በጥራት፣በጊዜና በመጠን የተለካ እንዲሆን አድርገው በማቀድ፣ እርስበርስ በመተሳሰር አንዱ ለአንዱ ግብዓት የሚያቀርብበትን ሂደት በመፍጠር የተጠናከረ ትስስራዊ የቅብብሎሽ የስራ ሂደትን በመከተልና ለሚያጋጥማቸው የግብዓት እጥረት መፍትሄ ማበጀት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ሀገራችን የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃዎችን ብቻ ሳይሆን እውቀትም በአግባቡ እየገዛች በመሆኑ በዘርፉ የታቀደውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናችንን አመላካች ነው ያሉት ሚኒስትሩ በድርጅቱ ውስጥ እየተሰራ ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሰው ሀብት ልማት ስራም አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አምራቾች ለቆሙለት ዓለማ ስኬት እውን መሆን፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣የውጭ ምንዛሬን ማዳንና ሌሎች ወሳኝ የሚባሉ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ የዜግነት ድርሻቸውን በመወጣት እንደ ሀገር የተያዘውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር በማሳለጥ እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ሰው ሀብት ልማት ላይ አበክረው መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

Share this Post