የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ወታደሮች በመሆን ለሀገራችንን ኢኮኖሚ ወሳኝ ሚና መጫዎት ይጠበቅብናል /አቶ መላኩ አለበል/

መስከረም 25/01/2015 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ አመራሮች፣ባለሙያዎች፣ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ባለቤቶች ዘርፉን በማዘመን፣ ሀገራችን ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ኃብት በመጠቀም የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ ምንጫችን አምራች ኢንዱስትሪውን መሰረት በማድረግ የማይናጋ የኢኮኖሚ ለመገንባት የኢንዱስትሪ ዘርፉ ወታደሮች መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ራሳቸውን በመጠየቅ ያሉባቸውን ክፍተቶች እንዲለዩ ፣የተጣለባቸውን ኃላፊነት በምን ደረጃ እየተወጡ እንደሆነ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ ወታደሮች ለመሆን የሚያግዙ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ጠቁመዋል፡፡

2014 በጀት ዓመት በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች የተፈጠሩበት ቢሆንም ችግሮችን በመቋቋም በሀገራችን ታሪክ በመጠንም ሆነ በዓይነት ከፍተኛ ምርት ወደ ውጭ በመላክ 500ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተመዘገበበትና ከ255ሺ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረበት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በቀጣይ የ2015 በጀት ዓመት የተሻለ የእቅድ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር መ/ቤቱ ከክልልና ከተማ አስተዳዳር ኢንዱስትሪ ቢሮ እና ከተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች ጋር የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጻም የግምገማና የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

Share this Post