በወጭ ንግድ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዕውቅና ተሠጠ፡፡

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም (ኢሚ) በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወጭ ንግድ ዕቅድ ለማሳካት ባስመዘገቡት የላቀ አፈፃፀም እና ለዘርፉ የማምረት አቅም በማሳደግ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች እውቅና ተሠጥቷል፡፡

በወጭ ንግድ በላቀ የወጪ ምንዛሬ ያስገኙ ክሪስታልና ሰርተፊኬት እንዲሁም ከዕቅዳቸው አንፃር ከ 90 በመቶ በላይ ያሳኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሰርተፊኬት ተሸልመዋል ፡፡

እውቅናና ሽልማቱ ለ2018 በጀት ዓመት የዘርፋን የወጭ ንግድ የዕቅድ ስኬት የተሻለ አበርክቶ የነበራቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ለማበረታታት እንዲሁም ሌሎችን ለበለጠ ውጤታማነት በማነሳሳት የቀጣይ የወጭ ንግድ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ አላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ለዘርፉ ሁለንታዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እያበረከቱ ላሉ የልማት አጋሮች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

የእውቅና ሽልማቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አበርክተዋል ።

Share this Post