አካታችና ዘላቂ የማኑፋክቸሪንግ ስርዓት መዘርጋት የፖሊሲው ቁልፍ የውጤት መስክ ነው (አቶ ጥላሁን አባይ)

ጥር 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአካባቢና በአየር ንብረት ለውጥ ስራ ላይ ለተወከሉ የክልልና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲውን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚው አቶ ጥላሁን አባይ አካታችና ዘላቂ የማኑፋክቸሪንግ ስርዓት መዘርጋት የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲው ቁልፍ የውጤት መስክ ነው።

በፖሊሲው ውስጥ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ዘላቂነትና አካታችነት እውን ለማድረግ አንድ ፕሮግራም እና ሁለት ንዑስ ፕሮግራሞች መለየታቸውንና ፖሊሲውን በመተግበር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ስኬታማነት ለማረጋገጥ አራት ስትራቴጅዎችና ሁለት ፍኖተ ካርታዎች ተጠናቀው ወደ ትግበራ መግባታቸውን ገልፀዋል ።

የአየር ንብረት ለውጥ ቡድን መሪው አቶ እስማኤል መሀመድ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለከባቢ አየር ተስማሚ እንዲሁም ለመጭው ትውልድ ደህንነትና ጤንነት የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ዘላቂና አካታች ዘርፍ እንዲሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪ ኢነርጅ ተመራማሪ የሆኑት አቶ መንገሻ አብርሃ እንደገለፁት የኢነርጅ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የስራ ሞተር ከመሆኑም በላይ የማምረት ሂደቱ እጅግ ውድ በመሆኑ የአጠቃቀም ስርዓታችንን በየጊዜው በመፈተሽና ሙያዊ ኦዲት በማድረግ የማሻሻያ ስራ መስራትና የዘርፉን ውጤታማነት ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post