በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በርካታ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት ሂደት ገብተዋል -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ህዳር 6/2015ዓ.ም አዲስ አበባ(ኢ.ሚ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላለፉት አመታት እንደ ሀገር በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ያጋጠሙ ቢሆንም ያጋጠመውን ፈተና መቋቋሞ ችሏል፡፡ በዚህም በ2014 በጀት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.16 ትሪሊዮን ወይም 126.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛው ግዙፉ እና ከሰሃራ በታች ካሉ አገራትም ሶስተኛው ኢኮኖሚ መሆን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

የ2014 ጂዲፒ እድገት 6.4 በመቶ እድገትየተመዘገበ ሲሆን በዚህ ዓመት 7.5 ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው አመት የተመዘገበው እድገት ከዘርፍ አንጻር ሲታይም የኢንዱትሪ ዘርፍ 4.9በመቶ የተመዘገበ ሲሆን በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከሲሚንቶ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው በአምራች ኢንዱስትሪው በተለይም እንደ ሀገር የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በርካታ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ማምረት ሂደት ያስገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Share this Post